ክርስትያኖ ኖናልዶ ሁለቱን ጎል። ጋሬዝ ቤል አንዱን። ሪያል ማድሪድ ከፒኤስጂ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ትላንት ጌታፌን የረቱበት ጥሩ ማሟሟቂያ ነበር።

ቤል በ24ኛው ደቂቃ ቀዳሚዋን ጎል ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ያገኘውን ኳስ አክርሮ መቶ አግብቷል።

የመጀመርያው አጋማሽ መጨረሻ ላይ ሮናልዶ ሁለተኛውን ጎል ለቡድኑ አግብቷል። ካሪም ቤንዜማ ያቀበለውን ቆንጆ ኳስ ይዞ ሁለት ተጨዋቾችን አልፎ አሪፍ ጎል አግብቷል።

የቀድሞው የኒውካስል እና ቼልሲ ተጨዋች ሎዊች ሬሚ ሁለተኛው አጋማሽ መጀመርያ ላይ ሁለተኛ ቢጫ አይቶ ቡድኑ ጌታፌን ወደ 10 ተጨዋች እንዲወርድ ምክንያት ሁኗል። ቢሆንም ጌታፌ በ66ኛው ደቂቃ ፍራንሲስኮ ፖርቲዎ ባገባው ፍጹም ቅጣት ምት የጎል ልዩነቱን ወደ አንድ መቀነስ ችለው ነበር።

ፔናልቲው ተገቢ አልነበረም። የማድሪዱ ተከላካይ ናቾ የሰራው ታክል ትክክለኛ ነበር።

ቢሆንም የጨዋታውን ውጤት የቀየረ ነገር አልነበረም። በ78ኛው ደቂቃ ሮናልዶ በጭንቅላቱ ግጭቶ ያገባት ኳስ የቡድኑን አሸናፊነት ያረጋገጠች ነበረች።

ማድሪድ ከመሪዎቹ ባርሴሎና 12 ነጥብ ርቀው ይገኛሉ።

5 መነጋገርያ ነጥቦች።

1) ጋሬዝ ቤል ታሪከኛው

ጋሬዝ ቤል በትላንትና ጨዋታ ሲሰለፍ በስፓኒሽ ላሊጋ 117ኛው ጨዋታው ነበር። ይህም ቁጥር 116ጊዜ የተሰለፈውን ዴቪድ ቤካምን አስበልጦ በስፔይኑ ውድድር አንደኛ የእንግሊዝ ተሰላፊ ተጨዋች እንዲሆን አስችሎታል።

በትላንትናው ጨዋታ ከኢስኮ የተቀበለውን ኳስ በማግባት ለቡድኑ 62ኛውን ጎል ማስቆጠር ችሏል።

በዚህ ጨዋታ በቀኝ በኩል እንዲጫወት ነበር የተመረጠው። ቤንዜማ ከፊት ሮናልዶ ከግራ። ቤል የግራ በኩል ተጨዋች ቢሆንም በትላንት ምሽት ጠንክሮ ሰርቷል።

2) ቀዝቃዛ ተጨዋቾችን

የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች በጨዋታው ቀዝቅዘው ነበር የሚጫወቱት። በሊጉ ያላቸው ተስፋ ትንሽ ነው።

መሪነቱን ከያዘው ባርሴሎና 1 ተጨማሪ ጨዋታ አድርገው በ12 ነጥብ ርቀው ተቀምጠዋል። ከሰርጂዎ ራሞስ በስተቀር ባርሴሎና ላይ እንደርሳለን ብሎ የሚጫወት ተጨዋች የለም።

አምስተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ሴቪያ በ9 ነጥብ ስለሚበልጡ ቻምፕዩንስ ሊግ ቦታ እናጣላን ብለው አይፈሩም።

በሊጉ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ትርጉም ስለሌላቸውም የመስላል የተመልካች ብዛት እምብዛም የነበረው። 55,106 ተመልካች ብቻ ነበር በስታድየሙ የተገኘው። ከ2013-2014 ውድድር አመት ጀምሮ እንደዚህ ጥቂት ሁኖ አያውቅም።

አንድ ተጨዋች ነበር ጎል ለማግባት ሲታገል የነበረው። እሱም…

3) ክርስትያኖ ሮናልዶ

የሮናልዶ አንደኛ ተጠቂ ቡድን ጌታፌ ናቸው።

ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት ሮናልዶ ጌታፌ ላይ 21 ጎሎች አግብቶ ነበር። ማድሪድ ከጌታፌ ጋር ባደረገው የመጨረሻ 7ግጥሚያዎች እያንዳንዱ ላይ አግብቷል ሮናልዶ። ትላንት 8ኛው ሁኗል።

በጨዋታው ላይ የመጀመርያ ጎሉ በቡድኑ ባለው ቆይታ የግሉ 300ኛ ጎል ነበረች።

ሌሎች ተጨዋቾች ቀዝቅዘው በረፈዱበት ምሽት ሮናልዶ ጎሎቹን እንኳ ሲያገባ ጭፈራው ልዩ ነበር።

በ33 አመቱ እንኳ በሚያገባቸው ጎሎች ከፍተኛ ደስታ ይነበብበታል። በአሁኑ ውድድር አመት 16 ጎሎች አሉት። በ23 ጎል በቀዳሚነት የሚመራው ሊዩኔል ሜሲ ላይ እየተቃረበ ነው።

በጨዋታው ሁለት ጎሎች ተሽረውበታል። አንዱ በኦፍሳይድ አንዱ ቤንዜማ በሰራው ጥፋት። ሮናልዶ በሁለቱም ሁኔታዎች ደስተኛ አልነበረም።

4) ሬሚ ቀይ አየ

ሎዊች ሬሚ ጥሩ አመታት እያሳለፈ አይደለም።

የቼልሲ ቆይታው በጉዳት ምክንያት አጭር ነበር። ለክሪስታል ፓላስ በውሰት ተሰቶ ቢሆንም እዛም በጉዳት ከሜዳ ርቆ ነበር።

ባለፈው አመት በቼልሲ ከተለቀቀ በኋላ ለላስ ፓልማስ ፈርሞ ነበር። አጀማመሩ ጥሩ ቢሆንም ከአሰልጣኙ ፓኮ ጄሜዝ ጋር በነበረው ጥል ቆይታው ጥሩ አልነበረም።

“እንደ ጭቃ ነበር የሚይዘኝ።” ሲል ስለ አሰልጣኙ ተናግሯል። ለቡድን ስብሰባ 1ደቂቃ በማርፈዱ የተቀጣው ሬሚ በደረሰበት ቀጣት ንዴት ውስጥ ገብቶ ነበር።

በመጨረሻ ለጌታፌ በውሰት ተሸጠ። ትላንት 6ኛ ጨዋታው ነበር። እስካሁን ለቡድኑ ማግባት አልቻለም።

በትላንትናው ጨዋታ ናቾን በክንድ በመምታታ በተሰጠው ሁለተኛ ቢጫ ከቡድኑ በጊዜ ተሰናብቷል።

5) የፒኤስጂ ነገርን አስመልክቶ

ማድሪድ ማክሰኞ ፒኤስጂን ይገጥማሉ። የመጀመርያውን ዙር ጨዋታ 3-1 ያሸነፉት ማድሪዶች በጉዳት የራቀውን ካሰሚሮን ወደ ቡድኑ ይመልሳሉ።

ለፒኤስጂ ጨዋታ ተብሎ ትላንት እረፍት የተሰጣቸው ተጨዋቾች ሉካስ ቫስኬስ እና ራፋኤል ቫራንን ያካትታሉ።

ማርሴሎም ከጉዳት ተመልሷል። ትላንት ከጉዳት መልስ ሲሰለፍ የመጀመርያው ጨዋታ ነበር። አጨዋወቱ ከጨዋታ እንደራቀ ተጨዋች አልነበረም። የሮናልዶን ሁለትኛ ጎል አሻግሮ ያቀበለው እሱ ነው።

ቶኒ ክሩስ እና ሉካ ሞድሪች ብቻ ናቸው ለጨዋታው በጉዳት የማይደርሱት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here