ሊዮኔል ሜሲ ያገባው አስደናቂ ቅጣት ምት በእሁዱ ጨዋታ ባርሴሎና አትሌቲኮ ላይ ወሳኝ ድል እንዲቀዳጅ ረድቶታል። ድሉ በሁለቱ ቡድኖች መሀከል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 8 አስፍቶታል።

ባርሴሎና ጨዋታውን በልጠው ነበር የጀመሩት። በ26ኛው ደቂቃ ሜሲ የመታው ቅጣት ምት ጎሉ እላይ ግርጌ ገብቶ ተቆጥሯል። የትላንትናው ጎል ሜሲ ለክለብ እና ለሀገር ያገባው 600ኛ ጎል ነው።

ለባርሴሎና ሁሉም ጥሩ ዜና አልነበረም። በጨዋታው መሳሳቢያው ላይ ጉዳት ያጋጠመው አንድሬስ ኢኒየስታ ተቀይሮ ወቷል። ማርች 16 ከቼልሲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ መሰለፉ አጠራጣሪ ነው።

ጨዋታው ከባድ ፉክክር የታየበት ነበር። ሁለቱም ቡድኖች ብዙ እድል መፍጠር አልቻሉም። ሉዊስ ስዋሬዝ እና ኬቪን ጋሚየሮ ያገቧቸው ጎሎች በኦፍሳይድ ተሽረዋል።

በውጤቱ ባርሴሎና ወደ ቻምፒዮንነት የሚወስዳቸውን ትልቅ እርምጃ ተራምደዋል።

5 መነጋገርያ ነጥቦች

1) ኢኒየስታ ችግር ላይ ነው

አትሌቲኮ አጨዋወታቸው ሀይል የተቀላቀለበት ነበር። በጨወታው ቀደም ብሎ ሳውል ኒጌዝ ጥፋት ሰርቶበት ነበር። ግን በ36ኛው ደቂቃ ሲቀየር በአትሌቲኮ ማድሪድ ተጨዋች ምክንያት አልነበረም።

በራሱ ጊዜ መሳሳብያውን ይዞ መሮጥ አቆመ። አሰልጣኙ ግን አልቀየረውም። ለተጨማሪ 10 ደቂቃ በሜዳ አቆይቶት በ36ኛው ደቂቃ በአንድሬ ጎሜዝ ቀየረው።

ለምን በሜዳ እንዳቆየው አይታወቅም። ምንም ሆነ ምን ለቼልሲው ጨዋታ መሰለፉን አጠራጣሪ አድርጎታል።

ከሜሲ በስተቀር እንደ ኢኒየስታ ኳሱን ለቡድኑ ይዞ የምያቆይ ተጨዋች በቡድኑ የለም። ከጉዳት በፍጥነት ካልተመለሰ ቼልሲ አድቫንቴጅ ይኖራቸዋል።

2) ሜሲ አሁንም መረቡን አግኝቷል

ሌላ ሳምንት ሌላ አዲስ ሬኮርድ ለሜሲ። በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ጊዜው 600ኛ ጎሉን ትላንት አግብቷል። ለባርሴሎና ደግሞ 539ኛውን።

ጎሏ ድንቅ ነበረች። በረኛው የተመታችውን ኳስ መንካት ችሎ ነበር። ኳሱ የተመታበት ጥንካሬ እና ኢላማ ለማዳን እንዳይቻል አድርጎታል።

ሜሲ በ3 ተከታታይ ጨዋታዎች 3 የቅጣት ምት ጎል ማግባት ችሏል። ባለፉት 30 አመታት እሱን እንደሬከርድ የያዘ ተጨዋች የለም።

በውድድር አመቱ 5 የቅጣት ምት ጎሎችን አግብቷል ሜሲ። ተቃራኒ ቡድኖች እሱን ከመጥለፍ ኳሱን ሳይቀሙት ቢተውት ሳይሻል አይቀርም።

3) የአትሌቲክ ኳስ

አትሌቲኮ የጨዋታ አጀማመራቸው ጥሩ አልነበረም።

በሁለተኛው አጋማሽ አንጌል ኮሬያ ተቀይሮ እስኪገባ ድረስ እዚህ ግባ የሚባል ሙከራ አልነበራቸውም።

ሲምዮኒ ጨዋታውን በ4-2-2 ፎርሜሽን ነበር የጀመረው። አራቱም አማካይ ተሰላፊዎች የመሃል አማካዮች ነበሩ። ክንፈኛ አልተሰለፈም። የተሻለ ኳስ ቁጥጥር የሰጠኛል ብሎ ነበር ያሰለፋቸው ሲምዮኒ። አልተሳካም።

የባርሴሎና ተጨዋቾች በልጠው መጫወት ችለዋል። ሲሚዮኒ ቆይቶ የአርጀንቲናዊውን አጥቂ ኮሬያ አስገብቶ ወደ 4-3-3 ፎርሜሽን ሲቀይር ጨዋታው የተሻለ ተከፍቶ ነበር።

4) ሁለቱ አመለኛ አጥቂዎች

ፕሪምየር ሊግ እያሉ በጉብዝናቸውም በአነጋጋሪ ጸባያቸውም የሚታወቁ አጥቂዎች የተሰለፉበት ጨዋታ ነበር። የባርሴሎናው ሉዊስ ስዋሬዝ እና የአትሌቲኮው ዲዬጎ ኮስታ።

ኮስታ ወደ ቀድሞው ክልቡ ከተመለሰ ጀምሮ የአጥቂ መስመራቸው አደገኛ ሁኗል። አንቶኒ ግሪዝማንም ወደ ቀድሞ ብቃቱ መመለስ ችሏል።

የባርሴሎናው ሉዊስ ስዋሬዝ በበኩሉ አመቱን በዋዠቀ አቋም ነበር ይጀመረው። አሁን ግን ወደ ቀድሞ ብቃቱ ተመልሷል። በሊጉ ካሉ ጨራሽ አጥቂዎች መልሶ ቀዳሚነቱን ይዟል።

በጨዋታው ግን ሁለቱም ተጨዋቾች በተከላካይ መስመሩ ተይዘው ነበር ያረፈዱት።

5) ግሪዝማን እምብዛም ነበር

አንቶኒ ግሪዝማን በባርሴሎና ሜዳ አግብቶ አያውቅም። ለማግባት ጉጉት ውስጥ እንደሆነ ተናግሮ ነበር።

በሁለተኛው አጋማሽ ያገኘውን እድል መጠቀም አልቻለም። ኳሱን ከአግዳሚው እላይ ነበር መለጋት የቻለው።

የተጨዋቹ የዝውውር ዋጋ 100ሚልየን ዩሮ ነው። በዚህ እንቅስቃሴው ብቻ ቢሆን ኖሮ ግን የሚገመተው ባርሴሎና ገንዘባቸውን ባላባኑ ያስብል ነበር።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here