ጋሪ ኔቪል እንደተለመደው ቼልሲን ክፉኛ ተችቷል። ምክንያቱን ከስር በሚታየው ቪድዮ ክሊፕ ማየት ይቻላል።

ቼልሲ ከተጋጣሚዎቻቸው ሲቲ ጋር ያሳዩት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ድክመት የታየበት ነበር።

በትዊተር ማህበራዊ ድህረ ገጽ ያሉ ተጠቃሚዎች ቼልሲን ክፉኛ ተችተዋል። አንድ ተተቃሚ የሚከተለውን የጨዋታ ቅንጫቢ ወስዶ የቼልሲን ጨዋታ ድክመት አሳይቷል።

የ18 ሰኮንዱ ክሊፕ እንደሚያሳየው ሴስክ ፋብሪጋዝ እና ዊልያን፣ የሲቲ ተጨዋቾች ፊታቸው ኳስ ሲቀባበሉ ቆመው ሲያይዋቸው ያሳያል።

የቼልሲ ተጨዋቾች መጫወት እንዳልፈለጉ ያሳያል። ኳሱን ለመንጠቅ ምንም አይነት ሙከራ አያደርጉም።

በቪድዮ የሚታየው ክሊፕ ጨወታው ለመጠናቀቅ 15 ደቂቃ ሲቀረው የነበረውን አጨዋወት ይሚያሳይ ነው።

ከሽንፈቱ በኋላ የቼልሲው አሰልጣኝ አንቶንዮ ኮንቴ የስካይ ስፖርት ዘጋቢ የሆኑትን ጋሪ ኔቭል እና ጄሚ ሬድናፕ ተችተዋል። ግን ዘጋቢዎቹ የቼልሲን አጨዋወት መተቸታው ተገቢ ነበር።

የቀድሞ ሊቨርፑል አማካይ ጄሚ ሬድናፕ እንዲህ ሲል አስተያየት ስቷል።

“የቼልሲ አጨዋወት ጸረ እግር ኳስ ነበር። እግር ኳስ ላይ ወንጀል ነው የሰሩት። ምንም ወደፊት መሄድ አልፈለጉም ነበር። ጨዋታው ሳይጀመር ነበር ቼልሲ የተሸነፉት።”

እንደ ጋሪ ኔቪል ደግሞ

“ቼልሲ ዛሬ ጨዋታቸው ላይ ፍራቻ ይነበብባቸዋል። ከአመት አመት ከከባድ ቡድን ጋር ሲጫወቱ ወደ ኋላ ተስበው እየተከላከሉ የሚጫወቱ ቡድኖችን አይተናል። ይህ ግን የተለየ ነበር። እንደ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ከሆነ እንቅስቃሴያቸውን ለመቀበል ትቸገራለህ። ከቡድኑ ፎርሜሽን ጋር አይገናኝም። ምንም ጥረት አለማሳየታቸው ነው ችግሩ።”

“እያቸው እስኪ። እዚህ ተቀምቼ ሳያቸው ሁሌ ትችት አብዝቼ ይሆን እንዴ ብዬ አስባለሁ። ይህንን ጨዋታ ግን በየትኛውም መልኩ አይተህ ትክክል ነው ማለት አትችልም።”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here