ኤድን ሃዛርድ ከሲቲው ሽንፈት በኋላ በገዛ ቡድኑ ታክቲክ ላይ ትችት ሰንዝሯል።

“3 ሰአት ሙሉ ብንጫወት ለውጥ አይኖረውም ነበር። ኳሷን መንካት አልችልም ነበር።”

በጨዋታው አልቫሮ ሞራታ ወደ ቤንች ተመልሶ ሲያረፍድ ሃዛርድ እሱን ተክቶ እንደአጥቂ ሁኖ ነበር የተሰለፈው።

ቼልሲ ይዞ የገባው አጨናጋፊ ታክቲክ አልሰራለትም። ሙሉ ጨዋታ አንድ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም። በኒኮላስ ኦታሜንዲ እና አይምሪክ ላፖርት ተይዞ የነበረው ሃዛርድ እዚህ ግባ የሚባል እንቅስቅሴ ማድረግ አልቻለም። በጨዋታው 1-0 ተሸንፈዋል።

ከጨዋታው በኋላ ሃዛርድ እንዲህ ሲል አስተያየት ስቷል።

“አሰልጣኙ ከፊት ሲያሰልፈኝ የተቻለኝን ሁሉ ጥረት አደርጋለሁ። ጥሩ ጨዋታ ለመጫወት ግን ይከብደኛል። በጨዋታው ኳሷን 3 ግዜ ብቻ ነው መንካት የቻልኩት።”

“ኳሱ ከኛ ጋር ስትሆን የተሻለ መንቀሳቀስ ነበረብን። በጨዋታው ጥሩ ያልሆኑ ውሳኔዎችን ስንወስድ ነበር። ብዙ እድል አልነበረንም። ግን ቢሆንም ባሉን እድሎች የተሻለ ነገር ማድረግ እንችል ነበር።”

“እድሎቻችንን ብንጠቀም ጎል ማግባት እንችል ነበር። ግን ተጋጣሚዎቻችን ሲቲ ነበሩ። እነሱ ጋር ማግባት ቀላል አይደለም።”

“ረጅም ኳስ ሲላክልኝ ለመዝለል ሞክሪያለሁ ግን ፍልሚያዬ ከኦታሜንዲ እና ላፖርት ጋር ነበር። የአየር ኳስ ከነሱ ላይ ማሸነፍ ቀላል አይደለም።”

“በለመድነው መልኩ አልተጫወትንም። ከፊት ጂሩ ወይም ሞራታ ቢጫወቱ ኖሮ በረጅም የተላኩ ኳሶችን የተሻለ መጠቀም እንችል ነበር። እኔ ስሆን ግን የቻልኩትን ብሞክርም ከባድ ነው።”

“ሜዳውን ለቀን ስንወጣ በጣም እንደሮጥክ የሰማሀል። ግን በዛውም ልክ ምንም እግር ኳስ የተጫወትክ አይመስልህም። የምያሳዝነው እሱ ነው። 3 ሰአት ብንጫወት ኳሱን አልነካውም ነበር። መጨረሻ ሰአት ላይ ነው የተሻሻልነው። በመጨረሽሻው 10-15 ደቂቃ ጨዋታውን መቆጣጠር ጀመርን። ግን ሙሉ ጨዋታ እንደዛ ነበር መሆን የነበረብን።”

“ከባርሴሎና ጋር የተወሰኑ እድሎች ነበሩን። ይበልጥ ማግባት እንችል ነበር። በዛሬው ጨዋታ ግን ምንም እድል አልነበረንም።”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here