ሊቨርፑል ፖርቶ ላይ የጀመሩትን ድል ያለ ችግር ጨርሰዋል።

ቡድኑ የመጀመርያውን ዙር 5-0 ያሸነፉለት ጀርገን ክሎፕ በጨዋታው ሞ ሳላን እና ቨርጅል ቫን ዳይክን አሳርፏል።

ቢሆንም ጨዋታውን ተቆጣጥረውታል። ፖርቶ በብቃት ያንሱ ነበር። ፈርተውም ነበር።

ለክሎፕ ሊከነክነው ይሚችል ነገር ቢኖር ከጨዋታ ብልጫቸው አንጻር የሚገባቸውን ጎል አለማግኘታቸው ነው። ሳዲዮ ማኔ ያደረገው ሙከራ የግቡን አግዳሚ መቶ ተመልሷል። ሌላኛው ሙከራው ለትንሽ ከአንግሉ ከፍ ብሎ ወቷል።

መጨረሻ ላይ ግን ለውጥ አልነበረውም። ሊቨርፑል በ10 አመት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ መጨረሻው 8 ደርሰዋል።

የጨዋታው 5 መነጋገርያ ነጥቦች

1) አዳም ላላና ለአለም ዋንጫው ይደርስ ይሆን?

ከመጀመርያው ዙር ውጤት አንጻር ለሊቨርፑል ተጨዋቾች ይህ ጨዋታ ተራ ጨዋታ ነበር። ከአደም ላላና በቀር። በጉዳት ከሜዳ ለራቀው ላላና ይህ ጨዋታ እንደ ፍጻሜ ነበር።

እንግሊዛዊው አማካይ አለም ዋንጫ የሚወስደውን እንቅስቃሴ ባገኘው እድል ሁሉ ማድረግ አለበት። ትላንት ያሳየው እንቅስቃሴ ያንን አላማ ያነገበ ይመስላል።

ላላና ከሌሎቹ አጥቂዎች በላይ ነበር። ለፊሚኖ፣ ለማኔ እና ሚልነር እድል ሲፈጥር ነበር ያረፈደው። ከጉዳት በፊት የነበረውን ሃይል እና ብቃት ምንም አላጣም።

የእንግሊዙ አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት ትጽእኖ ፈጣሪ ተጨዋቹን ያገኘ ይመስላል።

2) ከባድ ጨዋታዎች

ሊቨርፑሎች ለሚጠብቃቸውን ከባድ ጨዋታዎች ዝግጁ ይመስላሉ። ጀርገን ክሎፕ 5 ተጨዋቾችን አሳርፎም የቀዮቹ አጨዋወት በደንብ የተደራጀ ነበር።

ፖርቶ እንደገና ላለመሸነፍ ብለው ነው የገቡት። እንቅስቅሴያቸው የደከመ ነበር። በጨዋታው የሚስብ እንቅስቃሴ ይታይ የነበረው ከሊቨርፑል ብቻ ነበር። በሳድዮ ማኔ እድሎች ለጎል ተቃርበው ነበር።

3) ክሎፕ የሚመርጠው ሰው

የክሎፕ ችግር አሁን ማንን ልምረጥ ሳይሆን ማንን ላስወጣ ነው።

አሌክስ ኦክስሌ ቼምበርሊን በሳምንቱ የኒውካስል ጨዋታ አስደናቂ ነበር። ጄምስ ሚልነር በአውሮፓ ልዩ ነው። እዚህ የተሰለፈው ሚልነር ድጋሜ ጥሩ ነበር። በኦልድትራፎርድ ለመሰለፍ በሩን እያንኳኳ ነው።

ጆርጂኖ ዋይናልደምም ይመለሳል። ክሎፕ አማካዮች የተትረፈረፉበት ሰው ነው።

4) ሎቭረን ወይስ ማቲፕ

ውድድሩ ከኋላም ነው። ቪርጂል ቫን ዳይክ ባረፈበት በዚህ ጨዋታ ዴጃን ሎቭረን እና ጆዌል ማቲፕ ቀሪውን የቋሚነት ተሰላፊ ቦታ ለማግኘት ብለው ይመስላል አጨዋወታቸው ጥንካሬ የተሞላበት ነበር።

ሎቭረን በትንሹ የበላይ መሆን ችሏል። ማቲፕ ጨዋታው እንደተጀመረ በአየር የተላኩ የተወሰኑ ኳሶች አልፈውታል።

ሎቭረን ይልቁኑ ከቫን ዳይክ ጋር መጫወት የጠቀመው ይመስላል። በኮንፊደንስ ነበር የተጫወተው።

5) የሞ ሳላ ግቦች ተቋረጡ

መጨረሻ ላይ ተቀይሮ ግብቶ ነበር ሞ ሳላ። የባለ 32 ጎሉ አጥቂ ጎል ማግባት እንዲቀጥል እድል ተሰቶት ነበር።

15 ደቂቃ ቀርቶ ሲገባ ቡድኑን ከሽንፈት እንዲታደግ የሚቀየር ነበር የሚመስለው። ባለው አጭር ሰአት ጥሩ መንቀሳቀስ ችሏል። ጎል ግን አልሆነውም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here