አርሰን ቬንገር ከአርሴናል ቢለቅ ማን እንደሚቀጥረው ቢያስብ አይፈረድበትም። በአርሴናል ቦታው አደጋ ላይ ነው።

እስከ 2019 የሚያቆየውን ኮንትራት እስኪያበቃ መቆየት ቢፈልግም የ68 አመቱን አሰልጣኝ ፒኤስጂ ወደ ቡድናቸው ማምጣት እንደሚፈልጉ እየተዘገበ ነው።

የቬንገር ቡድን በ4 ተከታታይ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል። ከማንቸስተር ሲቲ ውጪ በኦስተርሱንድስ እና ብራይተን ተሸንፈዋል። በውጤቶቹ ምክንያት ደጋፊዎቹ በቬንገር ላይ ተነስተውበታል። አለቆቹም ተተኪ ሊሆን የሚችል ሰው እየፈለጉ ነው ይባላል።

ቬንገር በኮንትራቱ ገና 1 አመት ይቀረዋል። ቢሆንም ፒኤስጂዎች ቀጣዩ አሰልጣኛቸው እንዲሆን የተቻላቸውን እየሞከሩ ነው።

እንደ ቬንገር ግን ነገሮችን በአርሴናል መቀየር እችላለሁ ብሎ ያምናል። ዛሬ እንደወጡ ዘገባዎች ከሆነ ቬንገር ለቡድኑ አሰልጣኞች በራሱ ፈቃደኝነት ክለቡን እንደማይለቅ ተናግሯል።

ፒኤስጂ በአሁን ሰአት ኡናይ ኤምሬን በአሰልጣኝነት የያዘ ሲሆን ከቻምፕዮንስ ሊግ ውድድር ውጪ በመሆኑ አሰልጣኙን በአመቱ መጨረሻ ያሰናብታል ተብሎ ይጠበቃል።

ፒኤስጂ በትላንት ማታ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ ተሸንፈው ከውድድሩ ወተዋል።

በስፖርት ዊትነስ ጋዜጣ እንደተዘገበው ከሆነ የፒኤስጂው ፕሬዝደንት ናሰር አል ኬላይፊ ከቬንገር ጋር ኮንታክት ፈጥረዋል። በቀጣዩ አመት የክለቡ አሰልጣኝ ስለመሆን ያናግሯቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደሌሎች ዘገቦች ከሆነ የአርሴናል ተጨዋቾች እርስ በእርስ መጣላት ጀምረዋል።

ሜዙት ኦዚል፣ ሄንሪክ ምክታሪያን፣ እና ሽኮርዳን ሙስታፊ ተጠያቂ እንደተደረጉ ተገልጿል።

በቅርብ አዲስ ኮንትራት ከክለቡ ጋር የፈረመው ኦዚል ቡድኑን በሚችለው ደረጃ አልጠቀምክም ተብሏል። ምክታሪያን ደግሞ ያዝ የተባለውን ተጨዋቾች ባለመያዙ።

የጀርመኑ ሙስታፊ ደግሞ ጎሎቹን በሌሎች ተጨዋቾች ላይ በማሳበቡ ጥፋተኛ ተደርጓል።

ተከላካዩ ኼክተር ቤለሪን ከጨዋታው ውጪ መሆኑን የሰማው ጨዋታው ከመጀመሩ ከሰአታት በፊት በመሆኑ ቅር ተሰኝቷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here