ማንቸስተር ዩናይትድ መግዛት የሚፈልጓቸው የተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ የዋትፎርዱን አብዱላይ ዶኮሬን አካተቱ።

ከተጨዋቹ ፈላጊዎች ምሀከል ሊቨርፑል አርሴናል እና ቶተንሃም ይጠቀሳሉ።

የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኞች ቅዳሜ ዋትፎርድ ዌስት ብሮምን 1-0 በረታበት ጨዋታ በስታድየሙ ተግኝተው አይተውታል።

ጆሴ ሞሪንሆ ሁለት አማካይ ተጨዋቾች ወደ ቡድኑ መቀላቀል ይፈልጋል። በጁላይ ወር ማይክል ካሪክ 37 አመቱን ያከብራል። አመቱ መጨረሻ ላይ ጫማ ሰቅሎ የከለቡን አስልጣኝ ቡድን እንደሚቀላቀል ይነገራል።

ማሩዋን ፍሌኒም ቢሆን ክለቡን እንደሚለቅ ይዘገባል።

ዶኮሬ በአመቱ የዋትፎርድ ምርጥ ተጨዋች መሆን ችሏል። 30 ግዜ ተጫውቶ 7 ጎል አግብቷል።
የቡድኑ አንደኛ አግቢ ነው።

የ25 አመቱ ተጨዋች አካል ብቃት እና የኳስ ተሰጥኦ የማንቸስተሮችን አይን ስቧል።

ተጨዋቹ በዋትፎርድ ኮንትራቱ ሁለት አመት ይቀረዋል። በቅርብ ስለ ወደፊት ሃሳቡ ሲጠየቅ እንዲህ ብሏል።

“አመቱ ሲያልቅ እናያለን። እስከዛ ብንጠብቅ ይሻላል።”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here