ሊቨርፑል ለሞናኮ የሚጫወተውን ቶማስ ለማር ለመግዛት ተንቀሳቅሰዋል። እንደ ዘገባዎች ከሆን ከክቡ ጋር ወደ ስምምነት ተቃርበዋል።

ፈረንሳዊው ተጨዋች ስሙ ከሊቨርፑል ጋር ከተያያዘ ቆይቷል። ተጨዋቹን ሊቨርፑል በ145ሚልየን ፓውንድ ለባርሴሎና ለሸጡት ፊሊፔ ኩቲንሆ ተተኪ አድርገው ያዩታል።

አርሴናል ሌላ ተጨዋቹን የሚፈልግ ክለብ ሲሆን ከፈረንሳይ እንደሚወጡ ዘገባዎች ከሆነ ተጨዋቹን ለማስፈረም በሚደረገው ውድድር ሊቨርፑል ቀዳሚነቱን ይዟል።

ሞናኮ ተጨዋቹን ለመልቀቅ 88ሚልየን ፓውንድ የፈልጋል። እንደ ሊ10ስፖርት ጋዜጣ ዘገባ ሊቨርፑል ተጨዋቹን ለማስፈረም ጫፍ ደርሷል።

ጋዜጣው እንደሚያትተው ሊቨርፑል በቅርብ ሳምንታት ፈጣን እንቅስቃሴ አድርገዋል። ተጨዋቹን ለማዛወር የመጨረሻ ድርድር ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

ቶማስ ለማር ባለፈው አመት ለቡድኑ ያሳየው እንቅስቃሴ አድናቂዎች እንዲያፈራ አስችለውታል። በአመቱ 14ጎሎች ማግባት ሲችል ቡድኑ ፒኤስጂን በልጦ አንደኛ እንዲጨርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ባሁን ውድድር አመት ግን አቋም መዋዠቅ ይታይበታል። በ27 ጨዋታዎች 5 ጎሎችን ብቻ ነው ማግባት የቻለው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here