ሪዮ ፈርዲናንድ እና ፍራንክ ላምፓርድ ሊቨርፑል በቻምፕዩንስ ሊግ ብዙ መጓዝ ይችላሉ ብለው ያምናሉ።

ከፖርቶ ጋር የነበራቸውን ግጥምያ በመጀመርያው ዙር 5-0 መልስ ጨዋታውን ደግሞ 0-0 በማጠናቀቅ ወደ መጨረሻው ስምንት ማለፍ ችለዋል ሊቨርፑሎች።

በደርሶ መልስ ጨዋታዎቹ የጎልች ችግር እንደሌለባቸው ያሳዩት ሊቨርፑል በመከላከሉም ተሽለው ተገኝተዋል።

በቢቲ ስፖርት አስተያየቱን የስጠው ፈርዲናንድ እንዲህ ሲል አሞካሽቷቸዋል።

“ሙሉ ውድድሩን የመዝለቅ ብቃት አላቸው። ማንኛውም ቡድን ሊቨርፑልን መግጠም አይፈልግም።”

“ውድድሩ ውስጥ ማንም ሆንክ ይከብድሃል። እነዛን 3 ተጨዋቾች ስታያቸው በደንብ ሲጫወቱ በተለይ በአንፊልድ(ከባድ ስታድየም) በዛ ፍጥነታቸው ለማንም ከባድ ተጋጣሚ ነው የሚሆኑት።”

ላምፓርድም በፈርዲናንድ አስተያየት ተስማምቷል። እንዲህ ብሏል፡

“ለቻምፒዮንስ ሊግ የሚሆን ስታይል አላቸው። ከሜዳቸው ውጪ መልሶ ማጥቃት ተክነውበታል። በሜዳቸው ደግሞ በዛ ደጋፊ ፊት ማንንም ማሸነፍ ይችላሉ። ማንም እነሱን መጋጠም ይሚፈልግ አይኖርም”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here