ጁቬንትስ ቶተንሃምን በሜዳቸው 2-1 በማሽነፍ በድምር 4-3 አሸንፈው ወደ መጨረሻው 8 ዙር ማለፋቸውን አረጋገጡ።

ቶተንሃም አድቫንቴጅ ነበራቸው። በጁቬንትስ ሜዳ እኩል ነበር ውጤቱ። ሁለት ግብ ነበራቸው በጁቬንትስ ሜዳ። እዚህም በ3 ጨዋታ 6 ጎል ባገባው በሶን ሂዩንግ ሚን ጎል ቀዳሚነቱን ይዘው ነበር።

በሁለተኛው አጋማሽ ጁቬንትስ ጠንክረው መጫወት ጀመሩ። ስቲፋን ሊሽታይነር ያሻገረውን ኳስ ጎንዛሎ ሂግዋይን በማግባት ቡድኑን አቻ አደረገ። ብዙም ሳይቆይ የፓውሎ ዲባላ ጎል የቶተንሃሞችን የቻምፒዮንስ ሊግ ቆይታ በአጭሩ አስቀረ።

5 መነጋገርያ ነጥቦች

1) ቶተንሃሞች ገና ይቀራቸዋል

ከጨዋታው በፊት የቶተንሃሙ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ቶተንሃም በመሸነፍ እምነት መጫወት እንዳለባቸው ተናግረው ነበር። ክለቡን በአውሮፓ ውድድሮች ረዥም ርቀት መሄድ እንደሚችል ገለጹ።

በጨዋታውም አጀማመራቸው ጥሩ ቢሆንም የልምድ ማነስ እቅዳቸውን አሰናክሎባቸዋል። የጁቬንትስ ሁለት ጎሎች በ3 ደቂቃ ነው ተከታትለው የገቡት።

ቶተንሃም በአውሮፓ መድረክ እንዲሳካላቸው ግዜ እና ልምድ ገና ያስፈልጋቸዋል።

2) ጁቬንትስ ከአውሮፓ ቀንደኛ ቡድኖች አንዱ ናቸው

የጁቬንትስ ቡድን ልምድ ባካበቱ ተጨዋቾች ተሞልቷል። ልክ እንደ ሪያል ማድሪድ ትልቅ ጨዋታዎች ላይ ውጤት ማስመዝገብ ይችሉበታል።

የጁቬንትስ ጠባቂ 40 አመቱ ነው። ተከላካዩ ጆርጂዎ ቺየሊኒ 33። እያረጁ ቢሆንም ጨዋታ ለማሸነፍ ምን እንደሚያስፈልግ ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ያነሰ ቡድን ቢሆን 1-0 ሲመራ ተስፋ ይቆርጥ ነበር። ጁቬንትስ ግን ይለያል። የቻምፒዮንስ ሊግ ስኬታቸው ቁልፍ እሱ ነው።

3) የዌምብሊ ቲያትር

ቶተንሃም በአመቱ መጀመርያ አዲስ ስቴድየማቸው ግንባታ ሲያካሂድ ዌምብሊን ለ1 አመት ተከራይተዋል። አመቱ መጀምረያ ላይ በስታድየሙ ውጤት ርቋቸው ነበር። አሁን ግን በስታድየሙ ያለው ስሜት እንደራሳቸው ስታድየም ነው።

ስታድየሙ ለጨዋታው ልዩ ድምቀት ስቶታል።

4) ለአስቶሪ ክብር

የፊዮረንቲናው አምበል ዳቪድ አስቶሪ ድንገተኛ ሞት የጣልያንን እግር ኳስ አስደንግጧል። የ31 አመት ተከላካይ የነበረው አስቶሪ እሁድ በሆቴል በልብ ህመም በተኛበት ሞቶ ተገኝቷል።

ለተጨዋቹ ትውስታ ሁለቱም ቡድኖች ጥቁር አርምባንድ እጃቸው ላይ አጥልቀው ተጫውተዋል። ከጨዋታው በፊት ለ1 ደቂቃ ጸጥታ ስታድየሙ ዝም ብሎ ነበር።

5) ረዳቱ ዳኛ ከቪኤአር(ቪድዮ ዳኛ) ሳይብስ አይቀርም

ከሳምንት በፊት ቶተንሃም በኤፍኤካፕ ከሮችዴል ጋር ባደረጉት ግጥምያ የቪኤአር ስህተቶች ጨዋታውን አደብዝዘውት ነበር።

በዛሬው ጨዋታ ቪኤአር አልነበርም። ችግሩ የጎል ክልል ዳኛው ነበር።

ጃን ቬርቶንገን ደግለስ ኮስታን ግብ ክልል ውስጥ ጠለፈው። ለዛውም የጎል ዳኛው አይን ስር። ፍጹም ቅጣት ምት አልተሰጠም። ውሳኔው ለመረዳት የሚቸግር ነበር።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here