ማንቸስተር ሲቲ በሜዳቸው ከ15 ወር በኋላ ለመጀመርያ ግዜ ተሸንፈዋል። በመጀመርያው ዙር ተጋጣሚያቸው ባዝልን 4-0 ያሸንፉት ሲቲዎች ወደ መጨረሻው 8 ማለፍ ችለዋል።

በውድድሩ ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ማግባት የቻለው የባዝል ተጨዋች ማይክል ላንግ ለባዝል የአሸናፊነቱን ጎል አግብቷል።

በጨዋታው ቀዳሚነት የያዙት ሲቲ ነበሩ። ከጉዳት የተመለሰው ጋብርኤል ጄሱስ ለሲቲ ጎሉን አግብቷል። ከዛ ግን ተኙ ሲቲዎች። ብላስ ሪቬሮስ ያሻገራትን ኳስ ሞሃመድ ኤሊውኑሲ አገባ።

ጨዋታው በገፋ ቁጥር እየባሱ የመጡት ሲቲዎች በ71ኛው ደቂቃ ኤሊውኑሲ ያቀበለውን ኳስ ላንግ አግብቶ ባዝል ጨዋታውን አሸንፈዋል።

5 መነጋገርያ ነጥቦች

1) ጄሱስ ለሲቲ ተመልሷል

ጄሱስ ከቁርጭምጭሚት ጉዳት በተመለሰበት በመጀመርያው ጨዋታ ማግባት ችሏል። ፔፕ ጋርዲዎላ ለጨዋታው 6 ቅያሪ አድርገዋል። ሰርጂዎ አግዌሮ ከተቀያሪዎቹ መሃከል ነበር። በምትኩ የገባው ጄሱስ ለማግባት የፈጀበት ግዜ 8 ደቂቃ ነው።

በርናንዶ ሲልቫ ያሻገረለትን ኳስ ከመረብ አገናኝቷል። በአመቱ 11 ጎል አለው።

ጋርዲዎላ ወሳኝ ጨዋታዎች በተቃረቡበት በአሁን ወቅት የብራዚል ተጨዋቹ በመመለሱ ደስታ ይሰማዋል።

2) ፎደን ከፍተኛ ተስፋ አለው።

የ17 አመቱ የሲቲ አማካይ ፎደን አድናቂዎቹን የሚያበረክት እንቅስቃሴ አድርጓል።

የ10 ቁጥር ተጨዋች ቦታ ይዞ የተጫወተው ታዳጊ በጨዋታው አልደነገጠም። ኳስ አያያዙ ከእድሜው በላይ ነበር። ፔፕ ጋርዲዎላ በተጨዋቹ ትልቅ ተስፋ ጥለዋል።

የሲቲ የረጅም ግዜ እቅድ ከለቡ በሚያሳድጋቸው ታዳጊዎች ለመጫወት ነው። ፎደን ላይ ትልቅ ተስፋ ጥለዋል።

3) ጋርዲዎላ በቡድኑ ደስተኛ አልነበረም

ጋርዲዎላ ከጨዋታው በፊት ተጨዋቾቹን ፕሮፌሽናል እንዲሆኑ አስጠንቅቆ ነበር። ተረጋግተው ተጫውተው አመታቸውን የሚያቀዘቅዝ ሽንፈት እንዲያስተናግዱ አልፈለገም።

ባዝል አቻ የዳረገቻቸውን ጎል ሲቲ ሲያስተናግድ ንዴት በጋርዲዎላ ላይ ይታይ ነበር። ዳኒሎ ተመልሶ አልተከላከለም። ብላስ ሪቬሮስ በቀላሉ በርናንዶ ሲልቫን አልፎ ነበር ኳስ ያሻገረው።

ሁለተኛው ጎል ሲገባ ይበልጥ ብስጭት ይነበብበት ነበር ፔፕ።


4) ለያያ ቱሬ መጨረሻው ተቃርቧል

ቱሬ በወር ውስጥ ለመጀመርያ ግዜ መሰለፍ ችሏል። በአመቱ 7 ግዜ ብቻ ነው መሰለፍ የቻለው።

ጋርዲዎላ ከመጣ ጀምሮ ያያ በሲቲ የተገለለ ተጨዋች ነው። በተጨዋችነት ዘመኑ ለሲቲ ብዙ ቢያበረክትም ክለቡ የሱ ችሎታ ካስፈለገው ቆይቷል።

በአመቱ መጨረሻ ኮንትራቱ ሲያበቃ ሲቲን መልቀቁ አይቀርም። ባለው ግዜ ግን ለቡድኑ የአቅሙን ያደርጋል። ትላንትን ጥሩ ተንቀሳቅሷል።

5) የጋርዲዎላ ቢጫ ሪበን

የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበርን ህግ ላለመጣስ ኮቱ ላይ ያደረገውን ቢጫ ሪበን ላለፉት 3 ጨዋታዎች ሸፍኖት ነበር። በዛሬው ጨዋታ ግን እንዲታይ ብሎ ነበር የለበሰው።

የአውሮፓ ማህበር ከሪባኑ መለበስ ጋር ችግር የለበትም። የእንግሊዝ ማህበር ለምን ሪባኑን እንደከለከለ እንቆቅልሽ ነው የሆነበት ጋርዲዎላ። ሪባኑ በስፔይን ለታስሩ የካታሎንያ ግዛት ፖለቲከኞች ድጋፍ የሚያመለክት ነው።

ጋርዲዎላ ከአቋሙ አይመለስም። ማድረግ እቀጥላለሁ ብሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here