ቼልሲ እና አርሴናል ለናፖሊ የሚጫወተውን ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊን ማስፈረም ይፈልጋሉ።

የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች የሆነው ኩሊባሊ ላለፉት 4 አመታት በናፖሊ ትልቅ ተጨዋች መሆን ችሏል። በዚህ ውድድር አመት ናፖሊ አንደኛ ደረጃ እንዲቆናጠጥ ከቻለበት ምክንያት አንዱ የኩሊባሊ እንቅስቃሴ ነው።

ብዙ ፕሪምየር ሊግ ቡድኖች ተጨዋቹን የመግዛት ፍላጎት አሳይተዋል።

እንደ ሚረር ዘገባ የ26 አመቱን ተጨዋች ቼልሲ እና አርሴናል ይፈልጉታል። ማንቸስተር ዩናይትድም ተጨዋቹን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ክለቦቹ የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት የዝውውር ጥያቄ ያቀርባሉ። በአለም ዋንጫ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ዋጋው ሊንር ስለሚችል ከውድድሩ በፊት ተጨዋቹን ለመግዛት ይሞክራሉ።

ዩናይትድ በተጨዋቹ ላይ ያላቸው ፍላጎት በክለቡ ተጨዋች መልማይ ርናልድ ጃንሰን ይመካኛል። መልማዩ ጌንክ በነበረበት ወቅት ተጨዋቹን ወደ ክለቡ አምጥቶታል።

ጃንሰን አሁን የዩናይትድ ፍላጎት የሆነውን ሰርብያዊ አማካይ ሰርጄ ሚሊንኮቪች ሳቪች ገና 18 አመቱ እያለ ለጌንክ እንዲፈርም ማድረግ ችሏል።

ሚሊንኮቪች ሳቪች አሁን ለላዚዎ የሚጫወት ሲሆን በዘንድሮው ውድድር አመት በ35ጨዋታዎች 11 ጎሎችን በማግባት አድናቂዎችን አትርፏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here