ለቻምፒዮንስ ሊግ መጨረሻ 8 ከሚካፈሉት ውስጥ 4ቱ ታውቀዋል። ማንቸስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ ሪያል ማድሪድ እና ጁቬንትስ። 3ስቱ የቀድሞ እንግሊዝ ተጨዋቾች አንድ አሸናፊ ነው ያለው ይላሉ።

ሪዮ ፈርዲናንድ፣ ስቲቨን ጄራርድ እና ፍራንክ ላምፓርድ ጁቬንትስ ቶተንሃምን ካሸንፈበት ጨዋታ መልስ አስተያየት ሲሰጡ ውድድሩን ማን እንደሚያሸንፍ ተንብየዋል።

3ቱም ሪያል ማድሪድ ያሸንፋል ነው ያሉት።

የቀድሞ ተጨዋቾቹ የዚነዲን ዚዳን ቡድን በ5 አመት ውስጥ 4ኛውን ዋንጫ የመሸነፍ ጥንካሬ አለው ብለዋል።

ሪያል ማድሪድ በሃገራቸው ውድድር በ15 ነጥብ ባርሴሎናን ይከተላሉ። በአውሮፓ ግን የተለየ ቡድን ሁነው ነው የሚቀርቡት።

በጋሪ ሊኒከር ጥያቄውን ሲጠየቁ ፈርዲናንድ እንዲህ ብሏል – “ሪያል ማድሪድ። ልምዱ አላቸው። እና ሮናልዶ ሲጨመርበት ያሸንፋሉ።”

ጄራርድ በበኩሉ – “ሊቨርፑል እድል አላቸው ግን ሪያል ማድሪድን ነው የምጠብቀው።”

ላምፓርድ ከሁለቱ ጋር ተስማምቷል። “እኔም እስማማለሁ። ግን ለመተንበይ ይከብዳል።”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here