ሮሜሉ ሉካኩ እራሱን የጆሴ ሞሪንሆ “ሳርጀንት” ነኝ ሲል ተናግሯል።

በ75ሚልየን ፓውንድ ክለቡን የተቀላቀለው ሉካኩ ከአንድ ጨዋታ በቀር ዩናይትድ ባደረጋቸው ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በሙሉ ተሰልፏል። ለክለቡ 23 ጎል ማግባት ችሏል።

የ24 አመቱ ሉካኩ ሞሪንሆ በሱ የሚተማመነው የተባለውን ሁሉ እንደ ሳርጀንት ስለሚፈጽም ነው ብሏል።

ሉካኩ ለስካይ ስፖርት በሰጠው ቃለ መጠይቅ እንዲህ ብሏል።

“እኔ እንደሚመስለኝ አሰልጣኙ እኔን እንደ ሳርጀንቱ አድርጎ ነው የሚቆጥረው። ለአጥቂ የተለመደ ነገር አይደለም። ብዙ ግዜ አማካዮች ናቸው እንደዛ የሚታዩት።”

“ለቡድኑ ሁሌም ጠንክሬ እሰራለሁ። ለተስጠኝም እድል ሁሌም አመስጋኝ ነኝ። ግን መጨረሻ ላይ አጥቂ የሚገመገመው በጎሎች ነው። ማግባት እንዳለብኝ አውቃለሁ።”

“አሰልጣኙ ለኔ ጥሩ ነው። ለቡድኑ የወታደር አመለካከት እንዳለኝ ያውቃል።”

“ለቡድኑ ጠንክሬ በመስራቴ አሰልጣኙ ለማንኛውም ነገር እኔ ጋር መምጣት እንደሚችል ያሳያል። ሁልግዜም ቡድኑን ከራሴ በላይ አደርጋለሁ። እንደዛም ብዬ ነግሬዋለሁ። ቡድኑ ከምንም ነገር በላይ ነው።”

“በዚህ ክለብ ያየሁት ነገር ያለው የማሸነፍ ፍላጎት የተለየ መሆኑን ነው። ሁሌም ማሸንፍ እፈልጋለሁ። ዋንጫዎችን ማሳደድ እፈልጋለሁ። ከግል ዝና በላይ የማስቀምጠው ነገር ነው። ለዛም ይመስለኛል ሁሌም እንድጫወት የምመረጠው።”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here