አርሴናል ኤስ ሚላንን በሜዳው 2-0 በመርታት ውድድር አመታቸው ለመታደግ ተራምደዋል።

ሄንሪክ ምክታርያን እና አሮን ራምሲ ለአርሰን ቬንገር የጨዋታውን ሁለት ጎሎች አግብተዋል። ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ ጥሩ ውጤት ይዘው ወተዋል።

የምክታርያን ተጨርፋ የገባች ኳስ የጨዋታው የመጀመርያ ጎል ሁናለች።

የመጀመርያው ግማሽ ማለቅ ሲል አሮን ራምሲ አርሴናል የጀመሩትን ውብ እንቅስቃሴ ከኦዚል የተሻገረለትን ግሩም ኳስ ወደ በማግባት አርሴናልን በሁለት እንዲመራ አስችሏል።

የጨዋታው 5 መነጋገርያ ነጥቦች

1) የምክታርያን በአርሴናል የመጀመርያ ጎል

ይህ የምክታርያን በአርሴናል 8ኛ ጨዋታ ነበር። የተጨዋቹ አጨዋወት በጎል የተመረኮዘ ባይሆንም እስካሁን አለማግባቱ ጫን እንደሚፈጥርበት አያጠራጥርም።

ፈጥኖ ነበር የአርሴናልን የመጀመርያ ጎል ያገባው። የላካት ኳስ ተጨርፋ የሚላኑን ጠባቂ ዶኑራማ አለፈች። ምክታርያን ከግማሹ መጠናቀቅ በፊት ሁለተኛ ጎል የማግባት እድል አግኝቶ ነበር። የግብ አግዳሚውን ነበር ማግኘት የቻለው።

ለአርሴናል ከተጫወተባቸው ጨዋታዎች በሙሉ ምርጥ እንቅስቃሴ ያሳየበት ጨዋታ ይህ ነው። የአርሴናል ደጋፊዎች ወጥ አቋም ከአርሜኒያዊው ተጨዋች ይጠብቃሉ።

2) አርሴናል የአማካይ ፍልሚያውን አሸንፈዋል

አርሴናል ተከታታይ ሽንፈት ሲያሸንፉ አማካይ ክፍላቸው ዋና ተወቃሽ ነበር።

ፈጠራ አልነበረውም። ጥንካሬ አልነበረውም። ፍላጎት አልነበረውም።

እሱን በሙሉ በዛሬው ጨዋታ ቀይረዋል። ጃክ ዊልሸር ያላካለለው ሜዳ አልነበረም። ኳስ ይቀማል። ጥሩ ኳሶችን አመቻችቶ ያቀብላል።

አሮን ራምሲ እና ሜሱት ኦዚል ለሁለተኛው ጎል ግሩም ቅንጅት ፈጥረዋል።

ራምሲ አፈናጥሮ ለኦዚል የሰጠውን ኳስ ኦዚል መልሶ ሰንጥቆ ሰጠው። ራምሲ በረኛውን አልፎ ነበር ራምሲ ጎሉን ያገባው።

ከጨዋታው በፊት ኦዚል እና ምክታርያን በአንድ ቡድን መጫወት እንደሚችሉ ተናግሮ ነበር ቬንገር። በትላንትናው ጨዋታ እይታ አስተያየቱ ትክክል ነበር።

3) ሚላን ተራራ ተጋርጦባቸዋል

ሚላኖች ጨዋታውን የጀመሩት ከስኬት መልስ ነው።

የመጨረሻ 6 ጨዋታቸውን አሸንፈዋል። በ13 ጨዋታዎች አልተሸነፉም። ምክታርያን ከማግባቱ በፊት በ584 ጨዋታ ጎል አልገባባቸውም።

በትላንት ምሽት ግን ጥሩ አልነበሩም። አሰልጣኙ ጄናሮ ጋቱሶ መስመሩ ላይ እያበደ ነበር። መልበሻ ክፍል ውስጥ ምን እንደሚሆን መገመት ይቻላል።

በኤምሬትስ ውጤቱን መቀልበስ ይችሉ ይሆን?

4) ኦስፒና ቼክን እየተፈታተነ ይመስላል

ፒተር ቼክ 200ኛውን ጎል ያልተመዘገበበት ጨዋታ ለማድረግ ረጅም ግዜ እየጠበቀ ነው። አቋሙ ጥሩ እንዳልሆን እራሱ ተናግሯል።

በትላንቱ ጨዋታ ዴቪድ ኦስፒና አንድ ስህተት አልሰራም። በአውሮፓ በተሰለፈባቸው የመጨረሻ 3 ጨዋታዎች በሁለቱ ጎል አልገባበትም። አርሴናል ዋትፎርድ ከመጓዙ በፊት ቬንገርን እንዲያሰልፈው ሊጠይቅ ይችላል።

5) አርሴናሎች ለማንሰራራት እየተራመዱ ነው።

እዚህ ቢሸነፉ ኖሮ የአርሴናል አመት ይቋጭ ነበር። የቬንገርም ቆይታ አብሮት ያበቃል።

በካረባዎ ዋንጫ በአሳማኝ ሁኔታ ተሸንፈዋል። በኖቲንግሃም ፎሬስት እጅ ከኤፍ ኤ ካፕ ተሰናብተዋል። ምርጥ 4 ውስጥ የመጨረስ እድል የላቸውም።

በአመቱ የቀራቸው ነገር ቢኖር አውሮፓ ሊግ ነው። በሚቀጥለው አመት ቻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት ያልቸው 1 ተስፋ።

በሳንሲሮ 2-0 ማሸንፍ ሩብ ፍጻሜ አንድ እግር ማስገባት ማለት ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here