ኔይማር በመጪው ዝውውር መስኮት ወደ ባርሴሎና መመለስ ይፈልጋል. ፒኤስጂ መምጣቱ ስህተት እንደሰራ ያስባል.

ኔይማር በአመቱ መጀመርያ ከኑ ካምፕ ወደ ፓርክ ዴ ፕሪንስ የአለም ሬኮርድ በሆነ ሂሳብ ተዘዋውሯል.

ለአዲስ ክለቡ በ29 ጨዋታዎች 28 ጎል ማግባት ችሏል. ከድሮ ክለቡ ጋር ስሙ መያያዙ ግን አልቀረም.

የ26 አመቱ ተጨዋች በፈረንሳይ ቆይታው ደስተኛ እንዳልሆነ የዘገባል. ባርሴሎናን በመልቀቁ ቁጭት የሰማዋል.

እንደ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ዘገባ ኔይማር ለድሮ ቡድን አጋሮቹ ኑና ውሰዱኝ የሚል ጥሪ አስተላልፏል.

ባርሴሎናን ከሜሲ ጥላ ለመውጣት ብሎ የለቀቀው ኔይማር የፈረንሳይ ሊግ አጨዋወት ደከም ያለ እንደሆነ ያስባል.

የፒኤስጂ ቡድን አጋሮቹ በክለቡ እንዲቆይ ቢነግሩትም እሱ በ2019 መልሶ የባርሴሎና ተጨዋች መሆን የፈልጋል.

ኔይማር በአሁኑ ግዜ በጉዳት ከሜዳ ርቆ ይገኛል.

ቡድኑ በሪያል ማድሪድ 2-1 ሲረታ ያየው ኔይማር በማህበራዊ ሚድያ ለቡድን አጋሮች መጽናናት ተመኝቷል.

“በሽንፈቱ አዝኛለሁ. ቡድን አጋሮቼንም በሜዳ ሁኜ ማገዝ ባለመቻሌም አዝናለሁ. የሁሉንም ተጨዋች ጥረት ማየት አኩርቶኛል.”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here