አርሰን ቬንገር ቡድኑ ተመቶ የሚንገዳገድ ቦክሰኛ እንደነበረ ተናግሯል።

በትላንት የአውሮፓ ሊግ ጨዋታ ኤስ ሚላንን 2-0 መርታት የቻለው አርሴናል በቅርብ ሳምንታት ያሳየውን አቋም መዋዠቅ ማስተካከል ችሏል።

በማንቸስተር ሲቲ እና ብራይተን እጅ ለተሸነፈው አርሴናል የትላንትናው ውጤት እፎይታ የሚሰጥ ነው።

ከጨዋታው በኋላ ቬንገር እንዲህ ሲል አስተያየት ስቷል።

“የቅዠት ሳምንት ነበር ያሳለፍነው። ውጤቱ ጥሩ ነው። አልፈናል ብለን መዘናጋት ይለብንም። ጨዋታውን በሜዳችን መጨረስ አለብን”

ለአርሴናል ጎሎቹን ምክታርያን እና አረን ራምሲ አግብተዋል።

“በአጨዋወታችን ረክቻለው። በጨዋታው ጥሩ ምላሽ መስጠት ነበረብን። እስከመጨረሻው በደንብ ተከላክለናል። በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታችን ቀዝቅዞ ነበር ግን በ10 ቀን ውስጥ 4 ጨዋታ በመጫወታችን ይሆናል።”

“የዋንጫ ጨዋታ እሁድ ተጫውተህ ስተሸነፍ በአእምሮ ላማገገም የተወሰነ ግዜ ያስፈልግሃል። እኛ ግን ከ ሶስት አራት ቀን በኋላ መጫወት ነበረብን።”

ክለቡ እላይ ከተቀመጡት 4 ቡድኖች በነጥብ በመራቁ የአርሰን ቬንገርን ስራ መልቀቅ የሚጠይቁ አስተያየት ሰጪዎች ተበራከትዋል።

ቬንገር ግን የቡድኑን ተጋዳይ ስሜት አድንቀዋል።

“እንደ ቦክስ ጨዋታ ብታስበው ተመተህ እየተንገዳገድክ እያለ ስትመታ ማለት ነው። እኛ ላይ የተፈጠረው እንዲህ ነው።”

“ግን የሆን ሰአት ክብርህን መልሰህ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይኖርብሃል። ዛሬ እሱን ማድረግ ችለናል።”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here