ጆዜ ሞሪንሆ የአሌክሲስ ሳንቼዝን ምርጥ አቋም እየተጠቀመበት እንዳልሆነ ተናግሯል። ተጨዋቹ በሙሉ ብቃቱ እንዲጫወት እስከሚቀጥለው አመት እንደሚፈጅ ተናግረዋል።

ከአርሴናል በክረምት ውድድር መስኮት ከአርሴናል የተዘዋወረው ሳንቼዝ በሳምንት 500,000 ፓውንድ ደሞዝ የማንቸስተር ዩናይትድ አንደኛ ተከፋይ ነው።

የ29 አመቱ አጥቂ ለአዲስ ቡድኑ በ8ጨዋታዎች 1 ጎል ብቻ ነው ማግባት የቻለው። ሞሪንሆ ተጨዋቹ የመጣበት ሰአት መጥፎ ነው ብሎ ያምናል።

ሳንቼዝ እየከበደው ቢሆንም ማንቸስተር ከሊቨርፑል በሚያደርጉት የዛሬ ጨዋታ መጀመሩ አይቀርም። እንደ ሞሪንሆ ተጨዋቹ በሙሉ ብቃቱ እስኪጫወት ወራት እንደሚፈጅ ተናግረዋል።

ከሳንቼዝ እንዴት ጥሩ እንቅስቃሴ ማውጣት እንደሚቻል ተጠይቀው እንዲህ ሲሉ መልሰዋል ሞሪንሆ።

“እንደሱ አይደለም። የሱ ችግር የመጣበት ግዜ መጥፎ መሆኑ ነው። ክረምት ላይ ነው የመጣው። የክረምቱን መስኮት የማልወድበት ምክንያት ይህ ነው።”

“እሱን መግዛት ማጣት የማንፈልገው አጋጣሚ ነበር። በክረምቱ መስኮት ተጨዋች መግዛት አናምንበትም። በሚቀጥለው አመት የተሻለ እንደሚጫወት ጥርጥር የለኝም።”

“ከኛ ጋር እንዴት መጫወት አንዳለበት እየተማረ ነው። እኛም ከሱ ጥሩ አቋም ማውጣት እንዳለብን እየተማርን ነው። ቀስ በቀስ የሚሻሻል ነገር ነው። ከልምድ ጋር።”

“እንደ ድክመት አላየውም። እንደ ትልቅ እድል ነው የማየው።”

“ሜዳ ላይ ሀላፊንት ከመውሰድ ወደ ኋላ አይልም። ነገሮችን ከመሞከር ወደ ኋላ አይልም። እንደሚፈልገው ማጥቃት ሳይችል ወደ ኋላ ይመለሳል። ጨዋታ ለማደራጀት ይሞክራል።”

“ስህተት ሲሰራ ለማስተካከል ይሞክራል። ወደ ኋላ ተመልሶ ኳሱን መልሶ ለማግኘት ይጥራል።”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here