ማንቸስተር ዩናይትድ ዛሬ ከሊቨርፑል በሚያደርጉት ጨዋታ ፖል ፖግባ ሊያጡት ይችላሉ።

የአርብ ልምምድ በጉዳት ያቋረጠው ፖግባ የዛሬው ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ምርመራ ያካሂዳል። ምርመራውን ካለፈ የመጫወት እድል ያገኛል።

ዩናይትድ ያለ ዋና ተጫዋቹ ከገባ ለሁለተኛ በሚደረገው ፉክክር ሊሸነፍ ይችላል።

የጆዜ ሞሪንሆ ቡድን 3ኛ የተቀመጡትን ሊቨርፑል በ2 ነጥብ ብቻ ነው የሚመሩት።

ምንም እንኳ ፖግባ ከአሰልጣኙ ጋር በደንብ ባይግባባም ለጆዜ ሞሪንሆ ቡድን አሁንም ቁልፍ ተጨዋች ነው።

ፖግባ በአመቱ ለቡድኑ 26 ጨዋታዎች ተሰልፏል። 3 ጎሎች አሉት።

የማንቸስተር ተጨዋቾች ከጨዋታው በፊት ወደ ሆቴላቸው ሲገቡ ፖግባ አብሯቸው አልነበረም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here