የሉክ ሾ ማንቸስተር ዩናይትድ ቆይታ በግዜ ሊያበቃ ይችላል። በመጪው ዝውውር መስኮት ጆዜ ሞሪንሆ ተጨዋቹን ለመሸጥ ያኮበኮቡ ይመስላሉ።

ዩናይትድ ከሳውዝሃምፕተን በ2014 ተጨዋቹን ሲገዙ ለግራ ተከላካይ የአለም ሬኮርድ የሆነ 31.5 ሚልየን ፓውንድ አውጥተውበታል።

ከዛ ጀመሮ የ22 አመቱ ተጨዋች 61 ግዜ ብቻ ነው ለክለቡ መሰለፍ የቻለው። ጉዳትና ከአሰልጣኝ ጋር ጥል ተጨዋቹን ሜዳ ሰአት አሳጥተውታል።

እንደ ሳን ዘገባ ከሆነ ሞሪንሆ ሾውን ለቶተንሃም ሸጠው በምትኩ ዳኒ ሮዝን መግዛት ይፈልጋሉ።

የዩናይትድ አሰልጣኝ ተጨዋቹ ከድሮ አሰልጣኙ ከነበረው ከቶተንሃሙ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ጋር ያለው ጥብቅ ግንኙነት አላስደሰተውም።

ሾ አዲስ ጅማሬ ይፈልጋል። የዩናይትድ ቦታውን በአሽሊ ያንግ ተነጥቋል።

የ22 አመቱ ተከላካይ በዘንድሮ ውድድር አመት 6 ጨዋታዎችን ብቻ ነው መጀመር የቻለው። ከተጫወተባቸው 18 ጨዋታዎች 4ቱ ከታዳጊ ቡድን ጋር አብሮ ያደረገው ነው።

ሮዝም በዘንድሮው ውድድር አመት የመሰለፍ እድሉ አንሷል። ባለፈው አመት ቡድኑን የመልቀቅ ፍላጎት በማሳየቱ እና የክለቡን ክፍያ እርከን በመኮነኑ በቅጣት መልክ እንዳይጫወት ተደርጓል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here