በማርከስ ራሽፈርድ ሁለት ጎሎች ዩናይትድ ሊቨርፑል ላይ ድል ተቀዳጅቷል።

የእንግሊዙ አጥቂ ወደ ቋሚ አሰላለፍ በተመለሰበት ጨዋታ ሁለት ጎሎች ማግባት ችሏል።

በሁለተኛው አጋማሽ ኤሪክ ቤይሊ በራሱ ጎል ያገባው የሊቨርፑል ብቸኛ ጎል ሁና ተመዝግባለች። 6 ደቂቃ ጭማሪ ሰአት ቢኖርም ሊቨርፑል አቻ የምታደርጋቸውን ኳስ ማግኘት አልቻሉም።

ድሉ ዩናይትድን ቅርብ ተፎካካሪያቸው ላይ የ5 ነጥብ ልዩነት እንዲፈጥሩ ረድቷቸዋል።

የጨዋታው 5 መነጋገርያ ነጥቦች።

1) ተጽእኖ ፈጣሪው ራሽፈርድ

ማርከስ ራሽፈርድ ከመሃል አመት ጀምሮ ጨዋታውን የጀመረበት ግጥምያ ነበር። ለቡድኑ ያለውን አስፈላጊነት በግሩም መክፈቻ ግብ አሳይቷል። ቀጥሎም ሁለተኛ ጎል አክሏል።

ለመጀመርያው ጎል ከሮሜሉ ሉካኩ ጭንቅላት ተገጭታ የተሰጠችውን ኳስ ተቀብሎ የሊቨርፑሉን ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ በማለፍ አክርሮ የመታው ኳስ ጎል ሆናለች።

ለሁለተኛው ጎል ራሽፈርድ ጥሩ ኳስ ማንበብ አሳይቷል። ያመታትን ኳስ በጨረፍታ እርዳታ ጎል ስትሆን አይቷል።

ከአሌክሲስ ሳንቼዝ መምጣት ጀምሮ ራሽፈርድ የመሰለፍ እድል ርቆታል። በዚህ ጨዋታ ያለውን ፍጥነት እና የመጨረስ ችሎታ ድጋሚ ማሳየት ችሏል። ለዩናይትድ ከባድ መሳርያ ሊሆን ይችላል።

በጨዋታው አንድ ስህተት ብቻ ነው የፈጸመው። ጄምስ ሚልነር ላይ ጥፋት ሰርቶ ቢጫ ሲሰጠው።

2) ሉካኩ ወሳኝ ነው

100 ጎል የሚያደርሰውን ጎል ማግባት ባይችልም ሮሜሉ ሉካኩ በጨዋታው ድንቅ ነበር። የሊቨርፑል ተጨዋቾች ሊቋቋሙት አልቻሉም። በሁለቱም ጎሎች አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነበር።

በጭንቅላቱ የላካት ኳስ ነበረች የራሽፈርድ መክፈቻ ጎል የሆነችው። ሁለተኛውም ጎል አደረጃጀት ላይ የሉካኩ አስተዋጾ ከፍተኛ ነበር።

አካላዊ ጥንካሬውን፣ ፍጥነቱን በደንብ ተጠቅሟል። በሜዳ ላይ የማይታክት ስራው ይሚገባውን ያህል አይነገርለትም። ለቡድኑ ያለው ጠቃሚነት ከፍተኛ ነው።

3) ቤይሊ በተመለሰበት ጨዋታ ግሩም ነበር

ከዚህ ጨዋታ በፊት ኤሪክ ቤይሊ የተጫወተው ኖቬምበር 5 ዩናይትድ በቼልሲ 1-0 በተሸነፈበት ጨዋታ ነው። በቁርጭምጭሚቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ቀዶ ጥገና ማድረግ ነበረበት።

ቤይሊ የለምንም ጥርጣሬ የዩናይትድ ዋና ተከላካይ ነው። ከጉዳት እንደተመለሰ ሞሪንሆ በትልቅ ጨዋታ እሱን ማጫወት አልፈሩም። በጨዋታው ልዩ ነበር። የጨዋታው አንድ ጥፋቱ ኳስ አወጣለሁ ብሎ እራሱ ቡድን ላይ በስህተት ማግባቱ ነው።

ኳሷን ለማውጣት ሲሞክር እራሱንም ጎድቶ ነበር። ቢሆንም ጨዋታውን ከመቀጠል አላገደውም። ለቡድኑ የምያሳየው ፍላጎት ዩናይትድ እንዲያሸንፍ ዋነኛ ምክንያት ነበር።

የሱ መመለስ ለዩናይትድ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል። በቻምፒዮንስ ሊግ እና በኤፍኤካፕ በሚያደርጉት ጉዞ ይጠቅማቸዋል።

4) የሳላ ዝምታ

ሳላ ምንም እንኳ በውድድር አመቱ 32 ጎል አግብቶ ለአመቱ ምርጥ ተጨዋችነት እጩ ቢሆንም በዚህ ጨዋታ በአሽሊ ያንግ ታስሮ ነው ያረፈደው። ያንግ በጣም ጥሩ ነበር።

ያንግ በዚህ አጨዋወቱ ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን መልሶ መጠራቱ አይቀርም። በግራ ተከላካይ መስመር ካሉ የእንግሊዝ ተጨዋቾች በአሁኑ ግዜ ቀዳሚ ነው።

ያንግ ለጨዋታው ቁልፍ የሚባሉ የመከላከል ተግባራት ሲፈጽም ነበር። ሳላ የመታውን ኳስ በመከለል፣ ኳስ በማውጣት እና የተለያዩ ቦታውች በመጫወት ለቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች ሁኗል።

5) የዩናይትድ ጠንካራ ተከላካይ ክፍል

የሊቨርፑል ጎል ማሽን የሆነው አጥቂ መስመር በዩናይትድ ተገቷል። ማኔ፣ ሳላ እና ፊርሚኖ በዛሬው ጨዋታ አልሆነላቸውም።

ሳላ በያንግ ተይዞ ነው ያረፈደው። ማኔ እና ፊርሚኖ የለመዱትን ጨዋታ ለማሳየት ቦታ አልተሰጣቸውም። በሁለተኛው አጋማሽ አንቶንዮ ቫሌንሺያ በእጁ ያሶቆማት ኳስ ለሊቨርፑል ፍጹም ቅጣት ምት ታሰጥ ነበር። ቢሆንም ዛሬ የሊቨርፑል ቀን አልነበረም። መከላከል ላይ የሰሩት ስህተት አስከፍሏቸዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here