የሪያል ማድሪድ አምበል ሰርጂዎ ራሞስ ቅዳሜ ቡድኑ ከአይባር ጋር ባደረገው ጨዋታ የተፈጥሮን ጥሪ ሊያስተናግድ ለ5 ደቂቃ ጨዋታ አቋርጦ ወጣ።

ራሞስ እየሮጠ ከሜዳ ከወጣ ከ73ኛው ደቂቃ ጀምሮ ማድሪዶች ለ5 ደቂቃ በ10 ተጨዋች ነው የተጫወቱት።

የወጣበትን ምክንያት የተጠየቀው ዚዳን እንዲህ ብሏል።

“ራሞስ ሰገራውን መቆጣጠር አልቻለም ነበር። ሽንት ቤት መሄድ ነበረበት።”

በዛ ሰአት 3ቱንም ቅያሬያቸውን አድርገው የነበሩት ሪያል ራሞስን ቀይረው ማስወጣት አልቻሉም ነበር። ጨዋታው 1-1 እያለ ነበር ሁኔታው የተፈጠረው።

ሮናልዶ የአሸንፊነቱን ሁለተኛ ጎል ሲያገባ ወደጨዋታው ተመልሷል።

አትሌቲኮ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያላቸው ሪያልን በ4 ነጥብ ይመራሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here